Visit the new AsenaTv Website

https://asenatv.com

“ የተዳፈነ እሳት የጠፋ ይመስላል” – ክፍት ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዓቢይ ኣሕመድ

ክፍት ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዓቢይ ኣሕመድ “ የተዳፈነ እሳት የጠፋ ይመስላል” ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ኣቢይ ኣሕመድ፡ ሰላምታየን በማስቀደም፣ ባለፉት 6 ወራቶች የኤርትራ ኣምባገነን ፕረሲደንት ኢሳይያስ ኣፈወርቅን በማባበልና እንደ ሕጻን ልጅ ወዲ ኣፎም በማለት እሽሩሩ እያልክ የኤርትራ

ክፍት ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዓቢይ ኣሕመድ

“ የተዳፈነ እሳት የጠፋ ይመስላል”

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ኣቢይ ኣሕመድ፡ ሰላምታየን በማስቀደም፣ ባለፉት 6 ወራቶች የኤርትራ ኣምባገነን ፕረሲደንት ኢሳይያስ ኣፈወርቅን በማባበልና እንደ ሕጻን ልጅ ወዲ ኣፎም በማለት እሽሩሩ እያልክ የኤርትራ ህዝብ በማያምነውና በማይስማማበት የምታደርገው ሹክሹክታ ራስህን ከማታለል ኣልፈህ ለወደፊቱ ለኢትዮጵያና ለኤርትራ ህዝብ የማይጠቅሙና ኣደጋ ላይ የሚጥሉ የተንኮል ስራውች መሆናቸውን በቅድሚያ እንድታውቅ ይገበሃል።የኤርትራ ህዝብ ኣምኖና ተረድቶ በሚስማማበትና ልዑላዊነታችን ብሚያስከብር መንገድ ጎረቤታችን ከሆነችው ሃገር ኢትዮጵያና ህዝቧ በሰላም መኖር እንደምንሻ እንድታውቅልን እንፈልጋለን። ኣሁን በጀመርከው ይሉኝታ በሌለው መንገድ፣ኤርትራን በማይወክል ኣምባገነን መሪ ወክሎኛል በማለት ልዑላውነት ባላትና ነጻ በሆነችው ሃገር በማያገባህ ስራ ጣልቃ በመግባት ውሎችና ውሳኔዎች በማድረግ ላይ ስትገኝ የተሞኘን አንዳይመስልህ።ኣሁን ኣንተ የምትሰራው ያለህ ስራ ግን በሁለቱ ሃገሮች የነበረውና ለማገገም የተቃረበውን ቁስል ማከክ ካልሆነ በስተቀር ለሁለቱ ኣገሮች የሚያቀራርብና ዘላቂ መፍትሄ የሚያስገኝ እንዳልሆነ በቅድሚያ ልትገነዘበው ይገባል። በመጀመርያ ስልጣን ስትይዝ ሰላም፤ፍቅር፣ ብሚሉ ቅዱስ ቃላት ስትጀምር በቃልህ ኣምነን እያወቅን ተታልለን ነበር፣በኋላ ግን በሁለት ኣገሮች መካከል የሚደረገው ድንበር ሰው-ሰራሽ ነው ኣያስፈልግም፣ተደምረናል ኣንድ ሁነናል የሚል ኣነጋገርህ የተንኮል መሆኑን ስንረዳ፣ንግግርህ፣ጌና ከህልሙ ላልነቃ የኣማራ ክልል ህዝብ ስለ ኣንቃቃው፣ ኤርትራ ኣትገነጠልም፡ዓሰብን እናስመልሳታለን የሚል መፈክራቸው፣ኣንተም የምትደግፈው መሆኑን ልናውቀው የቻልን፣ክቡርነትህ “የሄዱትም ይመለሳሉ”በሚል ኣነጋግርህ ነው።እኔ የገረመኝ ግን ኤርትራ እንዴት እንደ ተገኘች እያወቅህ፣ካንተ ከተማርክና በትግል ካለፍክ መሪ ኣንደበት ስሰማ “ላም ኣለችኝ በሰማይ ወተትዋንም ኣላይ”መሆኑን እንዴት ልብ ኣላልክም? ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር የኤርትራ ጉዳይ ስላከተመ ለኣማራ ክልል ህዝቦችህ “ከወደቁ በኋላ መንፈራገጥ ለመላላጥ” ነው ብለህ ብትመክራቸው ይሻላል። የኤርትራ ህዝብ በመጀምርያ የሰላሳ ዓመት ጦርነት የሰዋቸው 65 ሺህ ምርጥ ልጆቹ፣ ቀጥሎም በወያኔ ግዜ ጦርነት የሰዋቸው ከ50 ሺህ ወጣቶች ከግዜ በሁዋላ ወደ ኢትዮጵያ እንመለሳለን ብሎ ይመስልሃልን?

ኣንተና ኣምባ-ገነኑ ኢሳይያስ የኤርትራ ህዝብና ሰራዊት የተዳከመ መስሎኣችሁ የምታደርጉት ፈንጠዝያ ሩቅ ሳትሄዱ የሚያሳፍራችሁ መሆኑንና ኣላማችሁም እግቡ ሳይደርስ በኣጭሩ እንደሚቋረጥ ልታውቁት ይገባል።ምክንያቱ የኤርትራ ሰራዊትና ህዝብ መታገስ “የተዳፈነ እሳት የጠፋ ይመስላል” ሲሆን፡ ክቡር ጠ/ሚኒስተር ትግርኛም ትንሽ ስለ ምትሞካክር “ዝተደጎለ ሓዊ ዝጠፍኤ ይመስል” ማለት ነው።ከብዙ ትግስት ብሁዋላ ግን ቀፎው እንደ ተነካ ንብ ለኣንተና ለኣምባ-ገነኑ ኢሳይያስ የሚነሳባችሁ መሆኑን መገንዘብ ኣትዘንጋ።የኤርትራ ህዝብ ለጊዜው በኣንባ-ገነኑ መሪ በኢሳይያስ እንኳ ቢሰቃይ፣ለህዝባችን ተስፋ የሚሰጥ ግን ኣንድ መሰረታዊ ሕግ ኣለ፡እርሱም ኣንድ ጨካኝ፣ ኣረመኔ፣እርኩስ መሪ ሊኖር እንደ ማይችልና፣ብዙም እንደ ማይቆይ ነው።

ስለዚህ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር፣በመጨርሻ ላሳስብህ የምፈልገው ያለ ምንም ቅድመ-ሁኔታ ድንበሩ ተከልሎ፣የኤርትራ ሰፊ ህዝብ የሚሳተፍበት የሁለቱ ኣገሮች ህዝብ በሰላም፣በመረዳዳት፣በመጠቃቀም የሚኖሩበት ዘለቄታ ያለው መፍትሄ እንዲገኝ ነው።

መሓረናዝጊ መርሃዊ የካቲት 8, 2019

aseye.asena@gmail.com

Review overview
2 COMMENTS
  • k.tewolde February 9, 2019

    It is a very well inked letter to the “I never had a clue there was this much dissent against Wedi Afe” looking PM.In critical times alliances define people,characters are revealed,you cant hide behind the retina detaching smile and pacifist words,INDA SAHAQKA DIRAROM WEDA’ALOM YU,This nation (ERITREA) have its owners,no matter what is happening today,sooner or later it will be claimed by them.Thanks M.M. Eritrea first and foremost!!

  • Danilo February 9, 2019

    ሳንፈልገው ወይም ሳንጠብቆው ሁሉንም ኣደጋ ላይ ነን።እነዚህ መሪዎሽ እሰያስ እና ኣቢይ እሳት ብሻ ጭሮው ልያስጨሩስን ከፈለጉ ዝምታችን በቃ!

POST A COMMENT