Visit the new AsenaTv Website

https://asenatv.com

“ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል” እንዳይሆንብህ

“ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል” እንዳይሆንብህ                ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ኣቢይ ስለ ኤርትራው ጉዳይ ኣስብበት!!! የማክበር ሰላምታየን ብማስቀደም፣ብህይወትህ ሰላምና ጤና፡ባለህ ከፍተኛ የስራ ሃላፊነትም የተቃና እንዲሆንልህ ልባዊ ምኞቴን ልገልጽልህ እወዳለሁ።                    

“ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል” እንዳይሆንብህ

               ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ኣቢይ ስለ ኤርትራው ጉዳይ ኣስብበት!!!

የማክበር ሰላምታየን ብማስቀደም፣ብህይወትህ ሰላምና ጤና፡ባለህ ከፍተኛ የስራ ሃላፊነትም የተቃና እንዲሆንልህ ልባዊ ምኞቴን ልገልጽልህ እወዳለሁ።                                                                                                                                                                                  ክቡር ጠ/ሚ. ኣቢይ የጠቅላይ ሚኒስተርነት ስራሕ ሀ ብለህ ስትጀምር፣በጣም ልብ በሚማርኩ ቃላት ሰላም፣ፍቅር፣ይቅር መባባል ብሚሉ ቅዱስ ቃላት መጀመርህ እንኳን ለኣገርህ ህዝብ ለኛ ለኤርትራዊያንም እንደ ጎረቤትና እህትማማች ኣገሮች በጣም ኣስደስቶን ነበር።ምክንያቱም  በእግዚኣብሔር ትእዛዝ ዘንድም ኣንደኛ ደረጃ የያዘው የእግዚኣብሔር ትእዛዝ፣እግዚኣብሔር ኣምላክህን ብሙሉ ልብ ማመንና ማፍቀር ሲሆን፣በሁለተኛ ደረጃ የሚቀጥለው ወንድምህን( ጎረቤትም ጭምር) እንደራስህ መውደድና ማፍቀር ስለሆነ።                                                                      በኢትዮጵያና ኤርትራ የተጀመረው የሰላም ለውጥ የሁለቱ ኣገሮች ህዝብ ተስፋና ምኞት የሚያሟላ ዘላቂ መፍትሄና እፎይታ የሚሰጥ መስሎን እጅግ በጣም ተስፋ በማድረግ በጉጉት ተጠባብቀናል።የተጀመረው የሰላም ሂደት ወይም ለውጥ ግን የኣምባ-ገነኑ መሪያችን የተደበቀና ስዉር ኣጀንዳ ማለት ኤርትራን የመሸጥና ህዝቧንም ለማጥፋት እውን ለማድረግ የታለመ መሆኑ ግልጽ እየሆነ ታይቷል።                                                                               የተከበርክ ዶ/ር ኣቢይ፣ ኣንተ ታጋይ ስለ ነበርክ የኢሳይያስ ኣፈወርቂ ጨቃኝ ባህርይና የኣረመኔ ተግባሮች ከነጻነት ትግላችን ጀምሮ በጣም የተማሩና ኣገር ሊመሩ የሚችሉ ወጣቶቻችን በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ  ኣዲስ ኣበባ በጣም የታወቁና ዝንስኞች የነበሩ ከእነ ብርሃነ-መስቀልና ዋልልኝ ብዙ የፖሊትካ እንቅስቃሴ ያደርጉ የነበሩ እነ ዮሃንስ ስብሃቱ፣ሙሴ ተስፋሚካኤል ዶ/ር ኢዮብና ሌሎችም የኤርትራ ነጻነት ከተገኘ በህዋላ በፕረሲደንትነት ስልጣን ተቀናቃኝ ወይም ተወዳዳሪዎች ይሆኑብኛል በማለት እንደገደላቸው ኣንተም በኤርትራ ሰውራ ታሪክ ውስጥ ሳታውቀው ኣትቀርም።  ኣምባ-ገነኑ ኢሳይያስ የኤርትራ አድገትና ብልጽግና እንደማይፈልግ ባለፉት 27 ኣመቶች በኤርትራ ስርኣተ-ኣልባ መንግስት ምን ያህል እንደ በደላት ኣንተ  በጉብኝት ወደ ኤርትራ ከሄድክ በሁዋላ ኣስመራ ከኣዲስ-ኣበባ ጋር ብማወዳደር ያች ትንሿ ሮማ ትባል የነበረችው ኣስመራ፣ብምን ደረጃ ላይ እንደ እንዳገኛሃት የዓይን ምስክር ነህ።                                                                                                                                        የደርግ መንግስት ከወደቀ በህዋላ በ27 የነጻነት ዓመቶች በኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋሙ ፋብሪካዎች፣ኢንዱስትሪዎች፣ኣውራ-ጎዳናዎች፣እንዲሁም በእያንዳንዱ ክልል ምን ያህሉ ዩኒቨርሲቶች ተከፍተው ስንት ምሁራንና ሊቃውንት እንዳፈራችሁ ላንተ መንገር ኣያስፈልግም።ኤርትራ ውስጥ በንጉስ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት የነበረችው ኣንዲት ዩኒቨርሲቲ ተዘግታ፣የቀሩት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ወደ ወህኒቤት ተቀይረው፣በኤርትራ ውስጥ ከትምህርት ቤቶች ይልቅ ወህኒ ቤቶች በቁጥር እንደ ሚበልጡ፣የኤርትራ ህዝብም ብእስርቤቶቹ እንደሚማቅቅ ልገልጽልህ እወዳለሁ።ምናልባት ለኣገሩና ለህዝቡ ነጻነት ለ30 ዓመቶች የታገለ ሰው እንዴት ብህዝቡ ላይ እንደዚህ ያለ ጭካኔ ያደርጋል  ትል ይሆናል፣ ኢሳይያስ ግን በኣሁኑ ግዜ ብትክክል የማያስብ የተዛባ ኣእምሮ ያለው መሆኑን ልብ ብለህ ይሆናል።ምክንያቱ ለኣንዲት ነጻነቷና ልዑላዊነቷ የተረጋገጠላት ኣገር ኣንተ ዶ/ር ኣቢይ ኣስተዳድረን ከእንግዲህ ወዲህ ኣንተ ነህ መሪያችን ሲል፣ትክክለኛ ኣእምሮ ካለው መሪ ሊወጣ የማይገባውና የማይጠበቅ ኣነጋገር ነው።

ክቡር ዶክተር፣ ስለ ህዝቦችህ ሰላምና መረጋጋት ስትል ኣለም በቃኝና ለሞት ሳይቀር የተፈረዱ ሰዎች ነጻ ስታወጣ፣የኛ ኣምባገነን መሪ ግን ያንተ ኣርኣያ ተከትሎ በትናንሽ ነገሮች  እንኳ መሻሻል እንዳያደርግ፣ያልሞሉ የነበሩ ወህኒ-ቤቶች በየቀኑ እየሞላቸው ይገኛል።ኣንተ ዶ/ር ኣቢይም ወዲ ኣፎም እያልክ እንደ ሕጻን ልጅ የማታለያ ቃላት ከምትጠቀም፣ኣንተ ለኣገርህ እንደምታደርግላት ያለህ ሁሉ፡ኣምባ-ገነን መሪያችን ባህርዩ እንኳ የማይፈቅድለት ቢሆን፣እስረኞች እንዲፈታ፣የመናገር፣የመጻፍ፣የሃይማኖት ነጻነት የህዝቡ መብት መሆናቸውን፣እንዲሁም በሕገ-ኣልቦነት ከሚያስተዳድር፣የኤርትራ ህዝብ ራሱ የሚተዳደርበት ህግ ስላለው እግብር ላይ እንድያውለው ብትመክረው ይሻላል።

ስለዚህ ክቡር ዶ/ር ኣቢይ ኤርትራን ከማይወክል ኣምባገነን መሪ በየግዜው የምታደርጋቸው ውሎችና ስምምነቶች ዲክታተሩ መሪያችን  ከወደቀ በህዋላ ፈራሽ መሆናቸውን በቅድሚያ ልታስብበት ይገባል።የኤርትራ ህዝብን የሚወክል ህዝባዊ መንግስት ሲመሰረት(ሩቅ ኣይሆንም) ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በኤኮኖሚ፣በፖሊቲካ በማህበራዊ ብማንኛውም ነገር ለሁለቱም ኣገሮች እስከ ጠቀመ ድረስ ተስማምተን እጅና ጓንት ሁነን ለመኖር የምንፈልግ መሆናችን እንድታውቅልን እንፈልጋለን። እንደ ታዘብኩህ የመንፈስ ሰው ትመስላለህ፣ኢትዮጵያና ህዝቧ ትጠቀም እንጂ ስለ ኤርትራና ህዝቧ ምን ቸገረኝ የምትል ኣይመስለኝም።ስለዚህ ብድጋሚ ላሳስብህ የምፈልገው ከዚህ  በፊት ከኢሳይያስ ጋር ያደረግካቸው ውሎችና ስምምነቶች ያለ ኤርትራ ህዝብ ፈቃድ  የተደረጉ ስምምነቶች በመሆናቸው ውድቅ እንድሚሆኑ፣ለወደፊትም ስምምነት ለማድረግ እቅድ ካለህ ያለ የኤርትራ ህዝብ ፈቃድ ተቀባይነት እንደ ማይኖራቸው ልታውቀው ይገባል።የኤርትራ ችግር ሳይፈታ ከኣምባ-ገነኑ ኢሳይያስ ጋር ዝም ብለህ በምታደርገው ሩጫ ግን በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ለወደፊቱ ኣለመግባባት የሚፈጥር መሆኑን ተረድተህ፣ “በሩጫ የታጠቁት፡በሩጫ ይፈታል”እንዳይሆንብህ መጠንቀቅ ይኖርብሃል፣ምክንያቱ በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል በነበረው ግጭት የዳነ ቁስል ከማከክ መቆጠብ እጅግ በጣም ኣስፈላጊ ነው።                                       ክቡር ዶክተር ኣቢይ ስለ ኣገርህና ህዝብህ ተቆርቋሪ በመሆን ጥሩ ስራ ጀምረሃል፣ለወደፊትም እግዚኣብሔር ከኣንተ ጋር ይሁን።የኤርትራው ጉዳይ እንደገና ሳታስብበት ብጀመርክበት መንገድ ከኣምባ-ገነኑ መሪ ብቻ የቀጠልክ እንደሆንክ ግን የኢሳይያስ የግል ስራ እንጂ ኤርትራን ወክሎ ስላልሆነ  ለኣንተም “ወጣ ወጣና እንደ ሸምበቆ ተንከባለለ እንደ ሙቀጫ” እንዳትባል እሰጋለሁ።

መሓረናዝጊ መርሃዊ

ጥቅምት, 2018

aseye.asena@gmail.com

Review overview
6 COMMENTS
  • Selam ina Fikr October 27, 2018

    Very good,

    Tigrewoch Amaregna by Chilu
    Teret ina Misalye Aytefachewem (Be Negusu gize yetemarut Amargna)
    say my Amhara friends

  • Gezae October 28, 2018

    You begged the derg and some of you sided with to destroy EPLF. You begged the Woyane regime to capture Asmara and ride the Woyane tanks, excavating our martyrs graves. You are begging Abiy for the same way for the same reasons, So I don’t need to repeat what has been said on your silly calls thread of choice. However, history does not repeat itself, either as tragedy or farce or anything else. Thus is that was made clear from the very beginning that no member state would interfere in the internal affairs of another. And only those matters would be discussed which concerned.

    Thankfully, that Eritrea and Ethiopia are taking the traction for a patriotic non-interventionism. Let us hope they will stand their ground on this matter; because a their duty is to address their own country’s problems and to provide solutions, not to take a moral high ground and to address another country’s problems. Thus why the visits of the PIA and then Prime Ministers Abiy accepted and have improved the situation.. As a result several agreements have also been signed.to restore peace and mutual trust between the two countries.

    I am against intervention in any shape or form in an idealized manner of pacifism in the way that is almost admirable (war is always bad after all)Eritrea has adopted a foreign policy of neutrality and non-involvement.The only argument that I sympathize with, like much of the public, is how the Eritrean government can deal with the Woyane Tigray to hand the so called opposition.

    • Negash October 28, 2018

      Eritrea has adopted a foreign policy of neutrality and non-involvement ~ Gezae.
      You must be reading PFDJ’s fiction books. Why are you still stuck with Woyane Tigray after all
      these years? Eritrea and Tigray are working together to destroy the Amara of Bekele and Gedu racist party. Dr Abiy will not last long in his position, the big game is between Tigray and Amara.

      • Gezae October 28, 2018

        Under international law, a treaty is any legally binding agreement between states/countries. A treaty can be called a Convention, a Protocol, a Pact, an Accord, etc.; it is the content of the agreement, not its name, which makes it a treaty. A government ratifies a treaty by depositing an instrument of ratification at a location specified in the treaty; the instrument of ratification is a document containing a formal confirmation that the government consents to the terms of the treaty. Sure the ratification process varies according to the laws and Constitutions of each country. For instance the Asmara-Eritrea Accord or the Rhiad-Saudi Arabia Accord

        Thus, unless a treaty contains provisions for further agreements or actions, only the treaty text is legally binding. Generally, an amendment to a treaty is only binding to the states that have ratified the amendment, and agreements reached at review conferences, summits, or meetings of the states parties are politically but not legally binding. An example of a treaty that does have provisions for further binding agreements is the UN Charter. By signing and ratifying the Charter, countries agreed to be legally bound by resolutions passed by UN bodies such as the General Assembly and the Security Council. Thus, UN resolutions are legally binding on UN Member States, and no signature or ratification is necessary.

        Confirming the recognition in the Strategic Partnership Agreement that cooperation between the Parties/governments/countries is based on mutual respect and shared interests; Emphasizing also the Strategic Partnership Agreement’s recognition that the Parties will go forward in partnership with confidence because they are committed to seeking a future of justice, peace, security, and opportunity for their people, as well as the reaffirmation of the Parties’ countries strong commitment to the sovereignty

    • Wedi Hagher October 28, 2018

      Gezae, you said

      “You begged the derg and some of you sided with to destroy EPLF. You begged the Woyane regime to capture Asmara and ride the Woyane tanks, excavating our martyrs graves. You are begging Abiy for the same way for the same reasons,”

      :”Woyo nata, ni hamata”

      You invited Weyane to Eritrean to help you evict ELF from the country, which costed us the lives of thousands..
      You made secret deals with Weyane and gave them Badme.
      You started a war with Ethiopia for no reason but to avoid implementing the constitution.
      You refused to discuss with Weyane demarcation of border to keep Eritrea on war footing for a decade.
      You gave them Aseb without the knowledge of the people and kept border demarcation on shelf for indefinite period, purposely, to keep peace on the Eritrean side pending for decades.
      All these crimes just to keep a monster in power.
      Gezae you are not less criminal than the man you are trying to protect.
      Shame on you.

  • Ermiyas October 29, 2018

    You are a zombie man. Who is going to read all this rubish? You wasting your time.

Post a Reply to Ermiyas Cancel Reply